አንድ ግራ የገባው አሜሪካዊ አባት ልዕልት መሆን የምትፈልግ ልጁን ምኞት ለማሳካት ሰሜን ሱዳን የሚገኝ መሬት ላይ አዲስ አገር ፈጠርኩ አለ


Princess_Emily-0d969.jpg22በዚህ ሳምንትየወጣው ዋሽንግተን ፖስት አስገራሚ ዜና ይዞ ብቅ በሎአል። በምስራቅ አሜሪካ በምትገኝው የቨርጂኒያ ግዛት ነዋሪ የሆነ አንድ አባት ልጁ በፊልም ላይ እንደምትመለከታቸው ልዕልቶች መሆን እንደምትችል ስትጠይቀው አትችይም ብሎ ሁኔታውን እንደማስረዳት ትችያለሽ እናሳካዋለን ይላል። በኋላም ልዕልት መሆን የምትችለው የሃገር መሪ ልጅ ስትሆን ብቻ ስለሆነ እራሱን የአንድ ሃገር ንጉስ ለማድረግ ያስባል። ይሄ ደግሞ ሌላ ችግር አመጣበት ምክንያቱም አሁን በአለማችን ላይ ያሉ ሃገራት መቼም ንጉስ እንደማያረጉት ስላወቀ አዲስ አገር መፍጠር አለበት ማለት ነው። አገር ለመስራት የሚያስፈልገውን መሬት ለማግኘት እስካሁን ያሉት ሃገሮች የማያውቁትን ቦታ ፍለጋ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ብቅ ያለው ጀርማያህ ሂተን የተባለው አባት ሰሜን ሱዳን ውስጥ የሚገኝ 200ሺ ሄክታር የሚገመት ሰው የማይኖርበት ባዶ ምድረ በዳ ያገኛል። ከዛም መሬቱን የሚያስተዳድረው ስለሌለ የኔ ነው በማለት እና “ሰሜን ሱዳን” የሚባል አገር ነው ብሎ በማወጅ አራት ኮኮብ እና ዘውድ ምልክት ያለበት ሰማያዊ ባንዲራ በቦታው ተክሎ ወደ አገሩ ተመልሷል። አሁን አገሪቷን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲኖራት የቀረው ነገር የጎረቤት አገሮቹን ፍቃድ ማግኘት ብቻ ሲሆን በዚህም ትብብር ለማግኘት ለአፍሪካ ህብረት ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። 🙂 🙂 ቂቂቂ 🙂 🙂 እቅዱ ተሳክቶ አገሪቷ እንደምትመሰረት ሙሉ እምነት ያለው ጀርማያህ ለልጁ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ስለሆነ ይህንን ያደረገው የአፍሪካ ፖለቲከኞችን በፍቅር አሸንፋቸዋለሁ እያለ ነው። ተጠባባቂ ልዕልቷ አገሩ የታወቀ የእርሻ ቦታ እንዲሆን ስለጠየቀች ይህም ከተሳካ በአካባቢ ያሉ መንግስቶች ሃሳቡን ሊቀበሉት ይችላል ብለው ያስባሉ

Advertisements

Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s